- በምናቀላፋበት ሰዓት 8ሚ.ሜ ( 0.3 ኢንች ) የማደግ ያህል ቁመት እንጨምራለን። በቀጣዩ ቀን ስንነቃ ግን ወደነበርንበት ቁመት ቀንሶ እንመለሳለን። ይህ የሆነው ልክ እንደ ስፕንጅ የሚጨመቀው ካርቴሌጅ ደስክ ስንቆም ወይም ስንቀምውጥ በግራቭኢቲ ትፅዕኖ ስለሚደርስበት ነው።
አክመል ሺፋ ከነቀምት
- ሰይጣን አቅም ሲያንሰው ሴትን ይልካል /ሞስኮብያዊያን/
- የልጃገረድ አባት ምንጊዜም እረኛ ነው
/ፈረንሳዮች/
- ወንድ ሲያፈቅር ይታወራል፡፡ ሴት ግን አጨንቁራም ቢሆን ማየቷ አይቀርም
/ግብፃዊያን/
- ገንዘብ ካለህ ሲኦል ውስጥ ጭማቂ ትጠጣለህ /ሊባኖስ/
- ወንዶች ሴቶችን የሚያፈቅሩትን ያህል ሰማያዊውን ዓለም ቢያፈቅሩ ኖሮ መላዕክት በሆኑ ነበር /ፈረንሳዮች/
- ለሴት ልጅ ቁንጅናዋን አንድ ጊዜ ንገራት ሰይጣን ደግሞ አስር ጊዜ ይደጋግምላታል
/ጣልያናዊያን/መስፍን ንጉሤ ከአዲስ አበባ
- ነጻ ልብ ረጂም እድሜ ትኖራለች.../አየርላድ/
- ገንዘብ ምርጥ አገልጋይ ነው ... /ህንዳውያን/
- ትዕግስት የሌለው በአጠቃላይ ምንም ነገር የለውም.../ጣሊያናውያን/
- ዝምታ በጥበብ ዙሪያ ያለ አጥር ነው.../ሃይቲዎች/
- ጆሮ ወደ ልብ የሚወስድ መንገድ ነው .../ፈረንሣውያን/
- ሁልጊዜ ማለት የሌለብህን ነገር ባለማለትህ ታሸንፋለህ.../ቻይናውያን/
- ፍላጎት እቅድን ያስተምራል.../አየርላንዳውያን/
ሄኖክ ሀብቴ ከቤቴ
ስህተትን መጠቆም እንጂ አሻሽሎ መሥራት አይክበድህ /ፕሎታሽ/
- መማርን ያቆመ መምህር የማስተማር መብት የለውም /ፔስታሎዚ-ጀርመናዊ/
- ሕይወት ሽንኩት ናት ከላይ ሲላጥላት ታስለቅሳለች /ሰንበርግ/
-- አሉባልታ ማለት ሁለትና ሁለትን ደምሮ አምስት ማድረግ ነው /ፓስካል/




No comments:
Post a Comment