ትርጉም ደረጀ መኰንን
አንፀባራቂውና ብርሃናማው የእመቤታችን መገለጥ በዋራቅ ከተማ በጊዛ ወረዳ በስሟ በተሰራው ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ለይ
ባለፈው ታኅሣሥ ወር በግብጽ ጊዛ ወረዳ በዋራቅ አልሃዳር ከተማ ውስጥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስሟ በተሰየመው ቤተክርስቲያን ጉልላት ላይ መጀመሪያ በብርሃናዊ አካል በተገለጠች ጊዜ የታየችው በዚህ ሁኔታ ነበር
ባለፈው ታኅሣሥ ወር 2002 ዓ.ም /December, 2009/ በግብፅ ካይሮ አልዘይቱን ከተማ ዋራቅ አልሀዳር በሚባል አካባቢ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስሟ በተሠራው ቤተ ክርስቲያን በግልጽ ለሕዝብ መታየቷን፤ እንዲሁም የግብፅ ኮፕት ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችንን በገሃድ መታየት እውነተኛነት ማረጋገጧን፤ በ«ሐመር» መጽሔት 17ኛ ዓመት ቁጥር 7፣ ጥር 2002 ዓ.ም እና በ«ስምዐ ጽድቅ» ጋዜጣ 17ኛ ዓመት ቁጥር 8፣ ከጥር 1 - 15 ቀን 2002 ዓ.ም እትሞቻችን በዜና መልክ ማቅረባችን ይታወቃል፡፡
ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በገሃድ መገለጥ በግብፅ የሚገኙ እና ሌሎችም ታላላቅ ዓለም አቀፍ ብዙኃን መገናኛ በስፋት ዘግበውታል፡፡ ይህንኑ የእመቤታችንን ተአምር በሰፊው ከዘገቡት ጋዜጦች መካከል በግብፅ ካይሮ እየታተመ የሚሠራጨው «ዋታኒ» /WATANI International/ ጋዜጣ አንዱ ነው፡፡ ለውድ አንባቢዎቻችን ሰፊ ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ «ዋታኒ» /WATANI/ ጋዜጣ በእሑድ ታኅሣሥ 11 ቀን 2002 ዓ.ም /20, December 2009, 11 Kyahk 1726, 3Moharram 1431, YEAR9 ISSUE 462/ እትሙ የዘገበውን ተርጉመን አቅርበነዋል፡፡

ከጊዛ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት የተሰጠ መግለጫ
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳይ ዘመን እና በጊዛው ሊቀ ጳጳስ አባ ዱማዲዮስ

የጊዛ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጽ/ቤት በታኅሣሥ ወር በዕለተ ዓርብ ታኅሣሥ 2 ቀን 2002 ዓ.ም /Friday 11, December 2009/ ልክ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በጊዛ ወረዳ በዋራቅ አል- ሃዳር ከተማ ውስጥ በምትገኘው በስሟ በተሰየመው ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ድንግል ማርያም በሙሉ ግርማ ሞገሷ መታየቷን ገለፀ፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም በሙሉ ቁመናዋ፣ የሚያንፀባርቅ መጎናፀፊያዋን ደርባ ፀአዳ የብርሃን ልብሷን ለብሳና ደማቅ ሰማያዊ ሰበኗን ታጥቃ የብርሃን አክሊል እንደደፋች በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉልላት አናት ላይ ረብባ ታይታለች፡፡ እመቤታችን የብርሃን አክሊልም በጭንቅላቷ ደፍታ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉልላት ላይ የሚገኙት መስቀሎችም ላይ አንፀባራቂ ብርሃን ይታይ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ ክርስቲያኑ ጉልላቶች መካከልና በበሮቹ አናት ላይ በሚገኙት ሁለት ማማዎች መካከልም ስትዘዋወር የአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ አንዳቸውም ሳይቀሩ አይተዋታል፡፡
የእመቤታችን መገለጥ አርብ ሌሊት ከሰባት ሰዓት እስከ አሥር ሰዓት ድረስ የዘለቀ ሲሆን ምስሏም በፎቶ ካሜራና በተንቀሳቃሽ ስልክ ካሜራ ተቀርጿል፡፡ ወደ ሦስት ሺሕ የሚጠጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ከአጎራባች ቀበሌዎች የመጡና ተላላፊ መንገደኞች በሙሉ በቤተ ክርስቲያኗ ዐውደ ምሕረትና ዙሪያ እንዲሁም በአቅራቢያው ጎዳና ላይ ተሰባስበው የእመቤታችንን በገሃድ መገለጥ በዓይናቸው አይተዋል፡፡
ከዕለተ ዓርብ /አመሻሹ ጀምሮ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዙሪያ የተከማቸው ምእመን /ሕዝብ/፣ ከምሽቱ በተለያዩ ጊዜያት ከቤተ ክርስቲያቱ አናት ላይ አንፀባራቂ ፀአዳ ርግቦች ከፍ ብለው ሲበሩ ያዩ ሲሆን በተጨማሪም ከገነት /ከሰማየ ሰማያት/ ከዋክብት በድንገት ተፈንጥቀው በመውጣት በአካባቢው እስከ ሁለት መቶ ሜትር ድረስ ሲወረወሩና ተመልሰው በድንገት ሲሰወሩ አስተውለዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ የተሰባሰበው ሕዝብ ለቅድስት ድንግል ማርያም መዝሙርና ምስጋና ያለማቋረጥ አቅርበዋል፡፡
ይህ ለቤተ ክርስቲያኗ እና ለመላው የግብጽ ሕዝብ ታላቅ ቡራኬ ነው፡፡ በረከቷና ምልጃዋ ሁላችንንም ይራዳን አሜን፡፡
ፊርማየእመቤታችን መገለጥ አርብ ሌሊት ከሰባት ሰዓት እስከ አሥር ሰዓት ድረስ የዘለቀ ሲሆን ምስሏም በፎቶ ካሜራና በተንቀሳቃሽ ስልክ ካሜራ ተቀርጿል፡፡ ወደ ሦስት ሺሕ የሚጠጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ከአጎራባች ቀበሌዎች የመጡና ተላላፊ መንገደኞች በሙሉ በቤተ ክርስቲያኗ ዐውደ ምሕረትና ዙሪያ እንዲሁም በአቅራቢያው ጎዳና ላይ ተሰባስበው የእመቤታችንን በገሃድ መገለጥ በዓይናቸው አይተዋል፡፡
ከዕለተ ዓርብ /አመሻሹ ጀምሮ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዙሪያ የተከማቸው ምእመን /ሕዝብ/፣ ከምሽቱ በተለያዩ ጊዜያት ከቤተ ክርስቲያቱ አናት ላይ አንፀባራቂ ፀአዳ ርግቦች ከፍ ብለው ሲበሩ ያዩ ሲሆን በተጨማሪም ከገነት /ከሰማየ ሰማያት/ ከዋክብት በድንገት ተፈንጥቀው በመውጣት በአካባቢው እስከ ሁለት መቶ ሜትር ድረስ ሲወረወሩና ተመልሰው በድንገት ሲሰወሩ አስተውለዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ የተሰባሰበው ሕዝብ ለቅድስት ድንግል ማርያም መዝሙርና ምስጋና ያለማቋረጥ አቅርበዋል፡፡
ይህ ለቤተ ክርስቲያኗ እና ለመላው የግብጽ ሕዝብ ታላቅ ቡራኬ ነው፡፡ በረከቷና ምልጃዋ ሁላችንንም ይራዳን አሜን፡፡
የጊዛ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ቪክቶር ሰላማ
ናዲር ሹክሪ
ናዲር ሹክሪ
በወርሃ ታኅሣሥ ዕለተ ሐሙስ /ለአርብ አጥቢያ/ ጥር 2 ቀን 2002 ዓ.ም /11th, December 2009/ ከዕኩለ ሌሊት አለፍ ብሎ በሀገረ ግብፅ በጊዛ ወረዳ በሰዎች በተጨናነቀችዋ ዋራቅ አል ሃዳር ከተማ በምትገኘዋ የቅድስት ድንግል እና የመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጣራና ጉልላት ላይ እንግዳ የሆነ ሰማያዊ ብርሃን ሲያንዣብብ በዕለቱ ተረኛ የነበሩ የቤተ ክርስቲያኒቷ ዘቦች ተመለከቱ፡፡
የአካባቢውን የመንገድ መብራት የዋጠው አንፀባራቂው ደማቅ ብርሃን በአካባቢው በሚገኝ ካፊቴሪያ እጅብ ብለው እየተዝናኑ የነበሩትን ሙስሊሞችንም ጭምር ትኩረት ማርኮ ነበር፡፡ በክስተቱ የተደመሙት እኒሁ ሙስሊሞች ደማቁ ብርሃን እየተሰበሰበ ወደ አንድ የሴት አካል ቅርፅ ሲቀየር አስተዋሉ፡፡ በአካባቢው ጎዳና በመጓዝ ላይ የነበሩ ጥቂት አማንያን ክርስቲያኖችም የሚያዩት ብርሃን የተወዳጇ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ውብ ምስል መሆኑ ወዲያውኑ ለመለየት ችለዋል፡፡ እመቤታችን ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ድረስ ብርሃን ለብሳ ብርሃን ተጎናጽፋ ወርቃማ አክሊሏን እንደደፋች ረዥም አብረቅራቂ ነጭ የብርሃን ቀሚሷንና ባለሰማያዊ ደማቅ መጎናፀፊያዋን ደርባ በቤተ ክርስቲያኑ ጉልላት አናት ላይ በሙሉ ቁመናዋ ተገልፃ ታየች፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ አናት ላይ እና በሁለቱ የቤተ ክርስቲያኗ ማማዎች መካከል ረብባ ስታንዣብብ የጉልላቶቹ መስቀሎች ብርሃን ማመንጨት ጀመሩ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ሁኔታ ዓርብ ከለሌቱ ሰባት ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ አስር ሰዓት ድረስ በስሟ በተሠራው ቤተክርስቲያን አናት ላይ እየተዘዋወረች ተገልጣ ታይታለች፡፡
የመገለጧ ዜና በከተማዋ ተሠራጨ፡፡ ሞባይል ስልክ በመጠቀም ጓደኛሞች መጠራራት ጀመሩ፡፡ ከፊሎቹ ይህን ትንግርት በቪዲዮ ካሜራ በመቅረፅ ለወዳጅ ዘመድ መላኩን ተያያዙት፡፡ ቀስ በቀስ የቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ በሰዎች ጎርፍ ተጥለቀለቀ፡፡ የዚያኑ ምሽት ቀደም ብለው ወደየቤታቸው የሄዱት የቤተ ክርስቲያኗ ቀሳውስት ተጠርተው የእመቤታችንን መገለጥ በዐይናቸው ለማየት በቁ፡፡ የጊዛ መስተዳድር የፖ¬ሊስና ፀጥታ ክፍል የዚህ ትንግርት ዜና እንደደረሳቸው ወደ ሥፍራው የፖሊስ ኃይል በመላክ ቤተ ክርስቲያኗን እንደ መቀነት ከበው ሲጠብቁና የታዳሚውን ደህንነት እና ሥነ ሥርዓት ሲያስከብሩ አደሩ፡፡
የእመቤታችን መገለጥ ዜና በእንደዚህ ሁኔታ በፍጥነት በመሠራጨቱ በቀጣዮቹ ጥቂት ሰዓታት የደስታ ሲቃ በተናነቃቸውና እጅግ በተደመሙ ታዳሚዎች ሥፍራው ተሞላ፡፡

የብርሃን እናቱ /እሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ/
የሚደንቀው ነገር የእመቤታችንን መገለጥ አይተው ዜናውን ያሠራጩት የአካባቢው ሙስሊሞች ነዋሪዎች መሆናቸው ነበር፡፡ በሉቃስ ወንጌል ላይም እመቤታችን ድንግል ማርያም «... እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ . . .» /ሉቃ.1-48/ ያለችው እንዲሁ እንዳልነበር ይህ ክስተት ያሳያል፡፡
ዋታኒ /WATANI International/ ሳምንታዊው የዕለተ ሰንበት ጋዜጣ የእመቤታችንን የመገለጥ ክስተት በትኩሱ ለመዘገብ ሪፖርተሮቹ በቦታው በአካል እንዲገኙ አድርጓል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቦታው በመገኘት ቤተ ክርስቲያኗን ከበው ነው ያደሩት፡፡ አጥንት የሚቆረጥመው የክያህክ /Kyahk/ የታኅሣሥ ወር/ ምሽት ብርድ ሳይበግራቸው ታዳሚዎቹ እስከሚቀጥለው ንጋት ድረስ ከበረከቱ ለመሳተፍ እሳት አንድደው እየሞቁ በዚያው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ከትመው ነበር ያደሩት፡፡ የምሽቱን አየር በነበረው የደስታ ድባብ ላይ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚቀርበው የማያቋርጠው መዝሙርና ምሥጋና ተጨምሮ አድምቆት ነበር፡፡ የምሽቱ ድባብ ሁኔታውን የንግሥ ክብረ በዓል ሲያስመስለው በተለይ ትኩስ የሚጠጣና የሚበላ ሳንድዊች ምግብ አዝዋሪዎችም ከወዲያ ወዲህ ተፍ ተፍ እያሉ ሲያስተናግዱ ለምሽቱ ድምቀት ሰጥተውታል፡፡ የምሽቱ ተአምር ታዳሚዎች የሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ስብስብ ነበር፡፡ ዓይነ ርግብ ያጠለቁ ሴቶች ዓይነ ርግብ ካላደረጉት ጎን ለጎን ቆመው ይታዩ ነበር፡፡ ሁሉም የእመቤታችንን መገለጥ በመደመም ይመለከቱ ነበር፡፡
ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ገደማ አንፀባራቂው ብርሃናማ የሴት ቅርፅ ያለው ምስል ከቤተ ክርስቲያኑ ጣራ ወደላይ ከፍ እያለ ከወጣ በኋላ በቤተ ክርስቲያኗ ማማና ጉልላት ላይ በድምቀት ረብቦ አረፈ፡፡ ሕዝቡ ደስታውን ከፍ ባለ ድምፅ «ድንግል ሆይ! ቅድስት ድንግል ተገለጠች!» እያለ እልልታውን ከዳር እስከ ዳር አቀለጠው፡፡ ባቅራቢያው ከሚኖሩ ጎረቤቶቻቸው መኖሪያ ቤቶች ጣሪያ ላይ በወፋፍራም ልብሶቻቸው ተጀቡነው ይህን ትንግርት ይመለከቱ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በጎዳናው ላይ የነበረውን ተመልካች ደስታ ለመጋራት ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅለው በአንድነት «የብርሃን እናቱ ድንግል ሆይ ቅድስት ሆይ፣ ትጎበኝን ዘንድ ሁሌም ወደኛ ነይ ነይ፡፡» እያሉ በአንድነት ዘመሩ፡፡
በፍቅሯ ይቃጠሉና በጭንቅና መከራ ተከበው የነበሩ ግብፃውያን ሁሉ አንዳቸውም እንኳ ተስፋ እንዳይቆርጡና እንዲጽናኑ ታበረታታቸው ዘንድ እናታቸው ቅድስት ድንግል ማርያም ከነሙሉ ክብሯና ከሚያስደምም ግርማ ሞገስ ጋር እንደገና ደግማ ተገለጠችላቸው፡፡

ገበርነ ሐሴት፣
ሐማዳ ሙሐመድ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ትይዩ በምትገኘው ካፍቴሪያ ውስጥ አስተናጋጅ ነው፡፡ «ዋታኒ» ጋዜጣ አነጋግሮት ነበር፡፡ ሐማዳ እና የቤተ ክርስቲያኗ የጥበቃ ተረኞች የእመቤታችንን መገለጥ በመጀመሪያ ያዩት የዓይን ምስክሮች ናቸው፡፡ «ሐሙስ ምሽት ታኅሣሥ 2 ቀን 2002 ዓ.ም /December 10,2009/ አምሽቼ እየሠራሁ ነበር፡፡ እኔና የሥራ ባልደረቦቼ በጣም ያስገረመንን ደማቅ የብርሃን ጎርፍ ተመለከትን፣» ይላል ሐማዳ ሙሐመድ፡፡ «ከዚያም ይህ ትንግርት ምን እንደሆነ እያሰላሰልን የቤተ ክርስቲያኒቱን ተረኛ ዘቦች ቀሰቀስናቸው፡፡ ወዲያውኑ ይህ ደማቅ የብርሃን ጎርፍ ቅርፅ እየያዘ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አናት ላይ አረፈ፡፡ ይህ ብርሃን ለቅጽበት ተሰወረንና እንደገና ተገለጠ፡፡ በአጠገባችን ቆሞ የነበረ አንድ ክርስቲያን «ይህች ቅድስት ድንግል ናት!» እያለ ጮኸ፡፡ ብዙ ሰዎችም መሰባሰብ ጀመሩ፡፡ ይህን ጊዜ ሰዓቱ ከለሊቱ ወደ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ይሆናል፡፡ ቅድስት ድንግል እንደገና በሙሉ ቁመናዋ ነጭ ብርሃናማ ቀሚስና ደማቅና ውብ ሰማያዊ መጎናፀፊያ ደርባ ተገልጣ ታየች፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ጣራና ጉልላት ላይ ከወዲያ ወዲህ እየተዘዋወረች ቆየች፡፡» እንደዚሁ ከዚህ በፊት አንድ ምሽት በሚያንፀባቁ በብርሃናማ ርግቦች ተከባ መገለጧ ይታወሳል፡፡ የዛሬውን ምሽት ተኣምር ለማየት የታደለው ሐማዳ ሙሐመድ ለ«ዋታኒ» ጋዜጣ ዘጋቢ፤ የቅድስት ድንግል መገለጥ ለክርስቲያኖችና ለሙስሊሞች ታላቅ ደስታ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ሐሰን ሙሐመድ /ሐሰን አንቦባ በመባል ይታወቃል/ የእመቤታችንን መገለጥ ካዩትና እማኝ ከሆኑት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች መካከል አንዱ ነበር፡፡ ሐሰን የጓደኛውን ሐማዳ ቃል የሚጋራ ሲሆን በተጨማሪም በሥዕለ ድንግል ማርያም ያየው እና አሁን ተገልጣ ያያት ድንግል ማርያም ፍፁም አንድ ዓይነት እንደሆነበት መስክሯል፡፡
ሌላው የዚህ ድንቅ ምሽት ታዳሚ የነበረውና ከጓደኞቹ ጋር በዚያች ካፍቴሪያ ቁጭ ብሎ ሲስተናገድ የነበረው ኡሰማ አቡ ሐዲድ የደስታ ሲቃ እየፈነቀለው፤ «የቅድስት ድንግልን ምስል በተንቀሳቃሽ /ሞባይል/ ስልኬ ካሜራ አንስቻታለሁ» በማለት ለ«ዋታኒ» ጋዜጣ አስረግጦ ተናግሮአል፡፡ ኡስማ በዚሁ ሳያባቃ «ብርሃኗ ከምሽት ጨረቃ የበለጠ እጅግ ውብ ነበር» በማለት ገልጿል፡፡
ይህን ተአምር ያዩ ሙስሊሞች በሙሉ ወዲያውኑ ክርስቲያን ጎረቤቶቻቸውን በመቀስቀስ የእመቤታችንን መገለጥ ሳያመልጣቸው እንዲያዩ አድርገዋል፡፡ ሙስሊም ጎረቤቱ ቀስቅሶት የነገረው የክርስትና ሃይማኖት አማኝ የሆነው አሸራፍ አብዱል ማላክ ወደ ጎዳናው ገስግሶ ታዳሚዎችን ለመቀላቀል አፍታም አልወሰደበት፡፡ አሸራፍ ዓይኑ ያየውን እንዲህ ሲል መስክሯል፡፡ «ከደመናት መካከል ሰንጥቆ የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን ቅድስት ድንግልን አጅቧት ከቤተ ክርስቲያኑ መንታ ማማ መካከል በሚገኘው መስቀል ላይ እመቤታችን ስታርፍ አየሁ፡፡»
ሌላዋ ሙስሊም የዋራቅ ነዋሪ «ድንግል ማርያም በቅዱስ ቁርአናችን ላይ የተከበረችና የተወደሰች ናት፣ በሁሉም ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች ዘንድ የተወደደች ናት» በማለት አሳቧን በደስታ ገልፃለች፡፡ አክላም «ለዚህም ነው በዋራቅ የምንገኝ ሁላችንም እጅግ የተደሰትነው፡፡» ብላለች፡፡

እርግጠኞች በሆንን ጊዜ
«ዋታኒ» ጋዜጣ የጠቅላላ ጊዛ /Giza/ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን አባ ቴዎዲዎስዮስን አነጋግሯቸው ነበር፡፡ የቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጣ መታየት የዋራቅ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት በስልክ ደውለው በነገሩኝ ጊዜ ማለትም በታኅሣሥ 3 ቀን /Deceber 11,2009/ እኔ በስተደቡብ ምዕራብ አሌክሳንድሪያ በማርዮት ወረዳ በምትገኘው በማር ሚና ገዳም ውስጥ ነበርኩኝ፡፡ ቀሳውስቱን የእመቤታችን መገለጥ ትክክለኛ መሆኑን እርግጠኛ እስክንሆን ድረስ አንዳችም መግለጫ በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳያወጡ ከማስጠንቀቂያ ጋር አጥብቄ መከርኳቸው፡፡ ምክንያቱም ያልተረጋገጠ ነገር እንዳይገለጽ ነው፡፡ ከዚያም ለሕክምና በአሜሪካ ለሚገኙት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ስለጉዳዩ አሳወቅናቸው፡፡ ቅዱስነታቸውም ካሉበት ቦታ ሆነው ሁኔታውን ከኛ ጋር በትኩረት መከታተል ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም፣ የቅድስት ድንግል ማርያም መገለጥ ትክክለኛ መሆኑ ሲረጋገጥና፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም መገለጧን እንዳዩ እርግጠኞች በሆንን ጊዜ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ ክርስቲያኗ መልእክት ታትሞ እንዲሠራጭ አደረግን፡፡
በጣም በሚያስደንቅ ሁኔታ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል መገለጥ በዋራቅ ወረዳ እንደተከሰተው ዓይነት ሁሉ በካይሮና በጊዛ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ያልተለመደ ብርሃንና በዛ ያሉ ርግቦች መታየታቸውን ነዋሪዎቹ እማኝነታቸውን መስጠታቸው ተዘግቧል፡፡

ጥርጣሬ
እዛው የሚያገለግሉ አባ ቢሻይ እንደሚሉት፤ በዋራቅ ወረዳ የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን የተቆረቆረችው አንድ በእግዚአብሔር ተጠርቶ ይኼን ዓለም ትቶ በመነነ ክርስቲያን በተለገሠች ቁራጭ መሬት ላይ ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ግን በዚህ ወረዳ የሚኖሩ ክርስቲያን ምእምናን ከአንዲት ፍርስራሽ ካታኰምብ /ዋሻ/ በስተቀር በውኑ ጸሎት የሚያደርሱበት ቦታ እንኳ አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም ግን በ2000 እ.ኤ.አ ቤተ ክርስቲያኗ ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል የግንባታ ፍቃድ አገኘች፡፡ አሁን የምትገኘውን ቤተ ክርስቲያን በ750 ካሬ ሜትር ላይ ሰባ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ግንባታዋ ከተጠናቀቀ በኋላ በቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሣይ ተመርቆ በአሁኑ ጊዜ ከሦስት ሺሕ ምእመናን በላይ እየተገለገሉባት ትገኛለች፡፡
ማሐር ናዝሚ ስለእመቤታችን መገለጥ የተለየ መንፈሳዊ እይታ አለው፡፡ «እግዚአብሔር እኛ የዋራቅ ወረዳ ምእመናንን ወደራሱ ያቀርበን ዘንድ ፈቅዶናል፡፡ አብዛኞቻችን ነጋዴዎች ወይም የአነስተኛ ፋብሪካ ሠራተኞች እንደመሆናችን ለእርሱ የምንሰጠው አንዳችም ጊዜ አልነበረንም፡፡ በቃ የዕለት ጉርሳችንን ለማሟላት ስንባክን ነው የምንውለው፡፡ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም መገለጥ በኋላ ግን፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ በአማኞች መጥለቅለቅ ጀምራለች»፡፡ በማለት ተናግሯል፡፡
የዋራቅ ቤተ ክርስቲያን ቄስ የሆኑት አባ ዳውድ ኢብራሂም ለ«ዋታኒ» ጋዜጣ ሲያስረዱ፤ «የእመቤታችን መገለጥ የሰላም መልእክትና የእርቅ ጥሪ ነው» ብለውታል፡፡
«የእመቤታችንን መገለጥ ዜና እንደሰማን ወዲያውኑ ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጉዳዩን አሳወቅን» ይላሉ አባ ዳውድ፡፡ «ሊቀ ጳጳሱም በተራቸው ዜናውን በሰሜን አሜሪካ /USA/ በሕክምና ላይ ለሚገኙት ለቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ አበሰሯቸው» አባ ዳውድ አክለውም፤ «ቤተ ክርስቲያኒቱ የተከሰተውን የእመቤታችንን መገለጥ ሁኔታ የዓይን እማኞችን ምስክርነት፣ የፎቶ ግራፍና የቪዲዮ ምስል መረጃዎችን ጨምሮ በጥንቃቄ መዝግባና መረጃ አጠናቅራ አጠናቃለች፡፡
እንዲህ ያለው ክስተት ተጠራጣሪዎችን የሚያበሳጭ ወይም ስሜታቸውን የሚያስቆጣ እንደሚሆን ይታወቃል፡፡ በተለይ የብዙኃን መገናኛ አውታሮች በሙሉ ሁኔታውን አለማመን ወይም ላለማመን መፈለጋቸውን አሳይተዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን፤ «ክርስቲያኖች እምነታቸውን ለማረጋገጥ የግድ የቅድስት ድንግል ማርያም መገለጥ ወይም ተአምራዊ መከሰት አያስፈልጋቸውም፤ ምክንያቱም እነሱ ቀድሞውኑ እምነታቸው የተመሠረተው በማይናወጸው አለት ላይ በመሆኑ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያላቸው እምነት እጅግ የጸና ነው፡፡» ብለዋል አባ ዳውድ፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና በረከት አይለየን አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

No comments:
Post a Comment