መድሃኔ Aለም ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ካለው ቤንዚን ማደያ ጋ ቆማ ታክሲ ትጠብቃለች። ሚስጥረ ትባላለች። ከቤንዚን ማደያው ጋር ተያይዛ ካለችው Aነስትኛ ቡና ቤት የሚወጡና የሚገቡ ደምበኞችዋ (Aብዛኞቹ መምህራን) Aይኖች ሳያርፉባት Aያልፉም። Eሷም ብትሆን ማስተዋሏ Aልቀረም። ሚስጥረ Aንደነዚህ ያሉትን ሰዎች "በAይንዋ ቂጥ" (በስዋ Aባባል) ነው የምትገረምማቸው።
ከወደ Aስኮ መስመር የሚመጡ ታክሲዎችን ትቃኛለች። Aጠገቧ ሊደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው የቀኝ Aጅዋን ሌባ ጣት ትቀስራለች። ሹፌሩ በተቀመጠበት መስኮት ትይዩ ታጎነብስና (ፒያሳ) ትላለች። ወደ ግራ ስትዞር በጆሮዎቿ ትክክል የሚቀረው የተፈጥሮ ጸጉርዋ ላይ የቀጠለችው ሰው ሰራሽ ጸጉር ጉንጉኖች በህብረት ወደ ቀኝ ይዘማሉ። ወደ ቀኝ ስትዞር ደግሞ ወደ ግራ። ምናልባት ልጭንቅላቷ ላለመታዘዝ ይሆን? ብቻ ባንድነት መዝመማቸውና ቀጥ ማለታቸው ከጥቁር ቀጫጭን ሽቦዎች የተሰሩ ያስመስላቸዋል።
ሁለት ታክሲዎች ሞልተው፤ ሶስተኛዋን ውይይት ጀርባ መቀመጥ ባለመፈለግዋ ኣሳልፋ፤ በAራተኛዋ ጉዞ ጀመረች። ባካል ወደ ፒያሳ በሃሳብ ወደ ኋላ። ስራ ለመቀጠር "ማመልከቻ" ያስገባችባቸውን መስሪያ በቶችና ሁኒ<_tawoc mastawes jemerec::
"Aይ ነቢያት! Eሱን በሎ ደግሞ ነቢይ! ነቢያት ብሎ ደግሞ ለሱ ስም! ስሙን ቄስ ይጥራውና! Aንደዛሬው በቅዳሚ_ ቀን ነው Aይደል ያኔ Eነሱ መስሪያ ቤት ስመላለስ! ‘ግድ የለሽም Aስቀጥርሻለሁ’ ብሎኝ የወጣሁለት! Eማዬ ትሙት Aንደሱ የተጫወተብኝ የለም! Aይ ምላስ!መቸም ያውቅበታል። Aኔማ በቃ Aሱ ሲያወራልኝ፤ በቃ የEውነት የተቀጠርኩ መስሎ ይሰማኝ ነበር። ምንዋ ሞኝ ነበርኩ ግን!
’ፈተና Aዘጋጅ ኮሚቴው ውስጥ ስላለሁበት ምንም Aትስጊ። በኔ ጣይው…’ ቅብጥርሶ ሲለኝ Eንዴት Aላምነው!? ማንም ቢሆን Eንዲህ ቢባል ያምናል። በሱ Aነጋገር፣ በዚያ ላይ Aለባበሱ! በቃ ልክ ባለስልጣን ነው Aኮ የሚመስለው። Aኔ ቢያንስ ቢያንስ ያንድ ክፍል ሃላፊ ይሆናል ብዬ ነበር የገመትኩት። Eረ Aሱማ ጉራው ስራ Aስኪያጅ ያስመስለዋል!
Aሁን Aሱን ትቶ ያን ኩሩሩ ድውይ ሰውዬ ማን ማኔጀር ነው ብሎ ይገምታል!? Aሁን በየነ ከዚያ ጉድ ባያወጣኝ ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር! Aይ በዩ ’Eንጋባ’ Aያለባይጨቀጭቀ Aሱው ይሻላል። Aግዜር ይስጠው Aሱ ባይኖረኝ ኖሮ ይኸኔ ዲቃላዬን ታቅፌ ቁጭ ብዬ Eቀር ነበር። Aይ በዩ ጤባው!
’ግዋደኛዬ ታማለችና ያን ሆስፒታል የሚሰራውን ግዋደኛህንAስችግርልኝ’ስለው፤’የትዋ?’Aንክዋን Aላለም። ግዋደኛውስራሱ ቢሆን ጥሩ ሰው ነው። ’ያንድ ቀን ስህተት ነው፤ ለበዩ Aትንገርብኝ፤ ችግሩ የራሴ_ ነው።’ስለው ’Aሺ’ ማለቱ። ግን ለበየነ ነግሮት ይሆን? Aልነገረውም። ነግሮትማ ቢሆን ኖሮ!
ግን ነግሮት ቢሆንስ ኖሮ፤ ምን Eንዳያደርገኝ! Aይፈልጠኝ፤ Aይቆርጠኝ!ግፋ ቢል መለያየት ነው! ላልጠፋ ወንድ! ግን Aሱው ሳይሻለኝ Aይቀርም። ምንም ቢሆን በወር ድሞዝ በተቀበለ ቁጥር የሚገዛልኝ ሽቶ፣ትያትር፣ሲኒማ መጋበዙ ራሱ፤ስንት ነገር Aለ!
Aንዳንዶቹማ ደረቆች! ጠብም Aይላቸው! በዩ ግን የምጠላበት ጸባዩ ’Aት ሊስት’ በሳምንት Aንዴ Aንኳን ’ናዪት ክለብ’ Eንግባ ብሎኝም Aያውቅም። ’ፓርቲ Eንሂድ’ስለው ከስንት Aንድ ቀን ነው የሚስማማው።’ዛሬ ፕሮግራሜ ….’የሚል ፈሊጥ Aለው።"
Eሱን ደስ የሚለው በየወሩ ገንዘቡን Eየከሰከሰ መደርደሪያ ሙሉከ ገጠገጠው መጽሃፍት Aንዱን Aንስቶ፤’ሚስጥር ይህቺን Aንብቢያት፤ ባለፈው ሰሞን የወጣች ቆንጆ መጽሀፍ ናት።’ማለት ነው። Eኔ ለራሴ Aንደማንበብ የሚያስጠላኝ የለም። ሳነብ Aንቅልፌ ይመጣብኛል።"
‘Eንቁላል ፋብሪካ’ Aየተባለ የሚጠራው Aካባቢ ደርሰው፤’ወራጅ ፣ ወራጅ Aለ!’ብሎ Aንዱ ተሳፋሪ ለመውረድ ታክሲዋ ስታቆም ነበር ከሃሳብዋ የነቃችው። ወዲያውታክሲዋ በርዋን ዘግታ ጉዞ ከመጀመርዋ ወደ ትውስታዋ ተመለሰች። ጎረምሳው የታክሲ ሹፌር ጉሮሮውን Aየጠራረገ ንግግር ለመክፈት ቢሞክርም Aልሰማችውም።
"ትሩፋት፤ ትሩፌ ነች ነብያት መዝገብ ቤት Aንደሚሰራ የነገረችኝ። ጎበዝ ናት።ፈተናውን Aልፋ የተቀጠረችው Eሷው ናት። ምነው የሷን ጭንቅላት ቢሰጠኝ! ነቢያት ሺፈራው የመዝገብ ቤት ጸሀፊ። ድንቄም የፈተና Aዘጋጅ ኮሚቴ Aባል! ከነቢያትስ ደመቀ ይሻላል። Eውነቴን ነው፤ ገገማ ቢሆንም ቁርጡን የሚናገረው ይሻላል። Aንደ ነቢያት ቀልጣፋ ቢሆንማ ኖር ይሄኔ_ ስንትዋን ያወጣ ነበር! ገና Aንድ ሁለት ቃላት ከመለዋወጣችን፤ ’የኔ Eህት ልረዳሽ የምችል Aይመስለኝም። መስሪያ ቤታችንም ቢሆን በዘመድ Aዝማድ የሚሰራበት Aይነት Aይደለም። ሊ_ላው ቢቀር በኔ በኩል የማይሆን ነገር ነው። ቦታው መመዘኛውን ለሚመጥን ማንኛውም Iትዮጵያዊ ክፍት ነው። ፈተና Eንሰጣለን፤ Aናወዳድራለን ማለት ነው። የውድድሩ Aሸናፊ ይቀጠራል። በዚህ መሰረት ነው ያንቺንም ጉዳይ የምመለከተው።’Aለኝ። ገገማ ነው።Aኔ ነኝ ያስተካከልኩለት፤ Eሱማ Aንደዚህ መናገርም Aይችልበትም።’ …............. ’በሳቅ ጦሽ ልል ምንም Aልቀረኝ! መቼስ ምን ላድርግ ለቅጥር Aመልካች Aይደለሁ፤ Aንደምንም ቻልኩት። በኋላ በዩ ነገረኝ ስድስት ኪሎ ማኔጅመንት ግራጁæየት ነው ብሎ። ከበየነ ጋር Aንድ ሁለት ቀን Aይቶኝ Aይደል ’…ሜሲሪያ ቤታቺኒ …’ያለው። በትውውቅ Aንደማይጠቅመኝ ማስጠንቀቁ ነው በሱ ቤት። ራሱ በየነስ ራሱ በየነስ ቢሆን ’ለምንልኝ’ብለው ’Eምቢ’ Aይደል ያለው! ’ፕሪንሲፕል’የሚሉት ነገር Aላቸው። Aይ ደመቀ! የኛ ሃቀኛ!’ኮከብ ሰራተኛ’ተብሎ ይሸለማታ!ግን ቢሆንም Eስው ቁርጤን የነገረኝ ይሻለኛል። ያኔማ ለፈተናም Aልሄድኩ፤ ላላፍ ነገር።
ራስ ደስታ ሆስፒታል Aካባቢ ሲደርሱ የታክሲው ሹፌር ሌላ የካሴት ክር Aስገባ።ሚስጥረን ’ካረቢያን ኪዊን’ የሚለው ሙዚቃ ወደ ለላ ትውስታ ቀየራት። የሹፌሩAይኖች Aጭሩ ጅንስ ቀሚስ በከፊል ያጋለጣቸው፤ ከጉለበቶችዋ በላይ Eስክ ቀሚሱ ጠርዝ ድረስ ያለው የሰውነት ክፍልዋ ላይ Aርፈዋል።Aላስተዋለቸቻቸውም።
"Aይ ዳኒ! ይሄኔ Aንተ Aሜሪካን ሀገር ተንደላቀህ ትኖራለህ። Eኔ Eዚህ በዚህ ሙዚቃ ሁሌ Aስታውስሃለሁ።’ካረቢያን ኪዊን’የሚለውን ቀይረህ ’Iትዮጵያን ኪዊን’Eያልክ ስትዘፍንልኝ የነበረው Aይረሳኝም። የሽኝትህ ቀን ዋዜማ ፌርዌል ላይ ስንት ጊዜ Eንደደነስንበት፤ ያልከኝ ሁሉ Aይረሳኝም።ይሄኔ Aንተ Eንክዋን ዘፈኑን Eኔንም ረስተህኝ የሆናል። Aይ ዳኒ! ’ዳኒ ቦይ በይኝ ስትጠሪኝ’ ያልከኝ ትዝ የልሃል?Eዚያ መቼም ’ዳኒ ቦይ’ Eያሉ ነው የሚጠሩህ። ’ሄሎው ዳኒ ቦይ! ሃው ዱ ዩ ዱ!’ Eንዴት ደስ ይላል!ታድለህ!Eኔም Aንድ ቀን ከዚች ሃገር መውጣቴ Aይቀር! ዳኒ ቃሉን ካላጠፈ ወደ Aሜሪካ Eወስድሻለሁ ብሎኝ ነበር። ቢሆን ነው Eንጂ ታድያ Eስከ ዛሬ ፖስት ካርድ Eንኳን ሰው Aይልክም?!
ቢሳካልኝማ ስራ፣ ምናምን ከማለት መውጣቱ ነበር የሚሻለኝ።"
’ካረቢያን ኪዊን’ Aብቅቶ ወደ ሌላ ትውስታ፤ ወደ ዋናው መለሳት። ግራ Eግርዋ ላይ የጫነችውን የቀኝ Eግርዋን Aውርዳ ግራ Eግርዋን የቀኝ Eግርዋ ላይ ጫነችው። የታክሲ ሹፌሩ Aይኖች Aረፉባቸው። Aላስተዋለቸቻቸውም።
"ከሁሉም የተጫወተብኝ ግን ደጀኔ ነው። Eሱ Eንደሸወደኝ ማንም Aልሸወደኝም። Eንደ ነበያት ስልጣን Aጥቶ Aይደለም። የሰራተኛ ክፍል ሃላፊ ነው Aሉ። ማስቀጠር ቢፈልግ በደንብ ይችል ነበር። መዸመርያ ጥሩ ሰው መስሎ ኋላ ማለት Aመጣ Eንጂæ^። ’Aይዞሽ ሚስጥረ ሁሉንም ነገር በኔ ጣይው፤Oኬ!’ከዚያ Eጆቹን ጠረጴዛ ላይ ደግኖ፤ ጣቶቸን Eያፍተለተለ፤ ቅንደቦቹን ሸብሽቦ፤ ከናፍሩን ወደፊት Eየለጠጣቸው፤ ’ግን ሚስጥረ Eንደምታውቂው Aንድ ሰው ላንድ ሰው Aንድን ጉዳይ ሲፈጽምለት በሌላ ጊዜ ያ ሰው፤ ማለቴ ጉዳዩ የተፈጸመለት ሰው በተራው ያን የፈጸመለትን የሚረዳበት ሁኔታ፣ መንገድ ካገኘ ወደ ኋላ Eንደማይል የምታውቂ የመስለኛል። Eና ተግባባን?….’Eኔ ልዽት Eንኳን ይህችንና የዝንብ ምንትስ Eናውቃለን Aልኩና በልቤ፤ ባፌ ’Eሺ!’ነዋ! መጀመሪያ Eኔ የሱ ጉዳይ ፈጻሚ ሆንኩ። Eሱ Eኔ Eርዳታ በምፈልግበት ጊዜ ወደ ኋላ Eንደማይል ሙሉ በሙ=ሉ በመተማመን። Aይ ደጀኔ! መጨረሻ ላይ ምናለኝ ታድያ?!’ሚስጥረ ምንም ማድረግ Aልችልም። ፍቅር ሌላ፤ ስራ ማስቀጠር ሌላ።’Aይን Aውጣ ደረቅ!Eሱን ብሎ ሃቀኛ!ስንትዋን Eንዲህ ብልዋት ይሆን? ታድያ ከሱ ደመቀ Aይሻልም?"
ታክሲዋ የማዘጋጃ በት ዋናው በራፍ ጋ ልትደርስ ትንሽ ሲቀራት ቆመችና ተሳፋሪዎችዋን ማራገፍ ጀመረች። ምንም Eንኳን ከስልሳ ሳንቲም በላይ የሚሆኑ ዝርዝር ፍራንኮች ቢኖርዋትም ሰሞኑን የምትመላለስበት መስሪያ ቤት ያስቀጥሩኛል ብላ ተስፋ የጣለችባቸውና ለዛሬ የቀጠሯትን የመስሪያ ቤቱን ምክትል ስራ Aስኪያጅ AEምሮዋ ውስጥ Aስገብታ ነበርና ቦርስዋን ከፍታ፤ ከተጣጠፉት ብሮች መሃከል Aንድዋን መዛ Aውጥታ ሰጠችው።
ሹፌሩ Aሁንም Aጭሩ የጅንስ ቀሚስ ወጥሮ ከያዘው ሰውነትዋ ላይ Aይኖቹን ሳይነቅል ተቀበላት። ከታክሲዋ ወርዳ መልስዋን ስትቀበል፤ AEምሮዋ ያለፉትን ጊዚያት ትቶ ላሁኑ ጊዚያት ክፍት ቦታ ስያገኝ፤ ሹፌሩን Aወቀችው። ’ጂ ሰ ስ!’ Aለች በሆድዋ። በሩን ’ጠርቅማበት’ Eርምጃዋን ቀጠለች።
Aሁንም የጎረምሳው ሹፌር Aይኖች ከበስተ ኃላዋ መቃኘታቸውን Aልተዉም። ከወራት በፊት የመዝገብ ቤት ጸሀፊ የነበረው፤ በAሁኑ ጊዜ ቤተሰቦቹ የገዙለትን ’ውይይት’ ታክሲ የሚያሽከረክረው የነቢያት ሺፈራው Aይኖች።
Aሁንስ ባታያቸውም Aስተውላቸዋልች።
ከጌቱ ሀይሉ
Followers
Blog Archive
-
▼
2010
(23)
-
▼
January
(22)
- crated by Girmay Reda
- ተአምረ ማርያም በግብፅ
- በጠበል ከሆዷ ውስጥ ከስምንት በላይ ነፍሳት የወጡላት ወጣት
- ልቦለድየሚስጥረ ማመልከቻዎች ከጌቱ ሀይሉ
- ጋሽ ገቢ ናፈቀኝ!!
- ማንኛውንም ገጽ ስለ ማዘጋጀት ወይም ስለ ማስተካከል ሌላ ጠቃሚ መረጃ በማዘጋጀት...
- ሀገርኛ ብሂሎች
- ከእንሳት ዓለም
- ይህን ያውቁ ኖሯል
- ''' ከመጽሐፍት ዓለም'''
- ከታላቆቹ አንደበት
- በሕይወታችን
- ቁጥሮች
- ''' ምርጥ አባባሎች'''
- እኔን
- የሰው ልጅ በአማካን በአንድ ቀን ውስጥ ...
- ማር ለጤና
- ከመጽሐፍት ገጾች
- ይህን ያውቁ ኖሯል
- ምክሮች
- 10 የስኬታማ ኢንተርፕርነሮች ችሎታዎች
- ከመጽሐፍት ገጾች
-
▼
January
(22)
Sunday, January 31, 2010
Subscribe to:
Post Comments (Atom)




No comments:
Post a Comment