ማር ለጤና
ማር በሺ የሚቆጠሩ ንቦች ለሰው ልጅ የሚያበረክቱት ሥጦታ ነው፡፡ ንቦች ከአያሌ አበቦች፣ ዛፎችና ሌሎች ተክሎች የቀሰሙትን ኔክታር በመቀመም ወደ ማር ይለውጡታል፡፡ ማር ማዕድናትን የተለያዩ ስኳሮችን እንዲሁም የብረት፣ የመዳብ የማንጋኒዝ፣ የፖታሺየም፣ የሶዲየም፣ የፎስፈረስ፣ የፕሮቲንና የቫይታሚን ርዝራዦች ያካብታል፡፡ ማር ለጤና በእጅጉ ጠቃሚ ነው፡፡
- አእምሮን ያጎለብታል
- ተውሳክን ከአንጀት ውስጥ ያራግፋል
- ድርቀትን ለማስወገድ ይረዳል
በጥዋት አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ቀምሰው ወደ ሥራዎ ይሰማሩ ሙሉ ቀን የደስታ ስሜት ያገኛሉ፡፡
ምን ግዜም ጥቅም ላይ ማዋል ያለብዎት ንፁሁን ማር ብቻ ይሁን ከገበያ የሚሸምቱት አልባሌ ማር ተጨማሪ የጤና ችግርን ከመፍጠር ባሻገር የሚፈይደው ነገር የለም፡፡
ንፁህ ማር ውሀ- 9 በመቶ፣ የፍራፍሬ ስኳር- 20 በመቶ፣ የወይን ስኳር- 15 በመቶ፣ ስኳር- 41 በመቶ፣ ማዕድናት- 10 በመቶ እና ሌሎች 5 በመቶ ይይዛል፡፡
ምንጭ፡- አዲስ ዘመን




No comments:
Post a Comment