Followers
Tuesday, August 9, 2022
የሹመት ዜና
አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከሥልጣን በተነሱት የቀድሞ የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ምትክ ለአምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) የኮሚሽነርነት ሥልጣን ሰጡ፡፡
የኮሚሽኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ ኮሚሽኑ የላከው ደብዳቤ አምባሳደር ሽፈራው (ዶ/ር) ከሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ኮሚሽነር ሆነው እንደተሾሙ አስታውቋል፡፡
አምባሳደር ሽፈራው (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትርና ትምህርት ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደርና እንዲሁም የሌሴቶና ናሚቢያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡
ምንጭ
Reporter
@EliasMeseret
Sunday, August 7, 2022
ኢትዮጵያ የደመቀችበት
በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው የአለም ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና በውድድሩ የመጨረሻ ቀን ኢትዮጵያ የደመቀችበት፣ የማይረሳ ታሪካዊ ምሽት!
3ኛው🥇ወርቅ በ1500 ሜትር ሴቶች ብርቄ ሀየሎም
4ኛው🥇ወርቅ በ800 ሜትር ወንዶች ኤርሚያስ ግርማ
5ኛው🥇ወርቅ በ5000 ሜትር ሴቶች መዲና ኢሳ
6ኛው🥇ወርቅ በ3000 ሜትር ወንዶች መሰናክል ሳሙኤል ዱጉና
4ኛው🥈ብር በ5000 ሜትር ሴቶች መልክናት ውዱ
5ኛው🥈ብር በ3000 ሜትር ወንዶች መሰናክል ሳሙኤል ፍሬው
ድንቅ ምሽት፣ ኢትዮጵያ ከፍ ያለችበት፣ በደቂቃዎች ውስጥ በተለያዩ ውድድሮች ወርቅ የጠራረገችበት ድንቅ ምሽት፣ 4 ወርቅ 2 የብር ሜዳሊያዎችን በሰዓታት ውስጥ! (via Temesgen Yifru)
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውድድሩን ከአሜሪካ እና ጃማይካ በመቀጠል በሶስተኛነት አጠናቃለች።
እንኳን ደስ አላችሁ፣ አለን!
ምንጭ
@EliasMeseret
Subscribe to:
Posts (Atom)