Facebook o girmay reda

Powered By Blogger

Followers

Tuesday, August 9, 2022

የሹመት ዜና

አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከሥልጣን በተነሱት የቀድሞ የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ምትክ ለአምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) የኮሚሽነርነት ሥልጣን ሰጡ፡፡ የኮሚሽኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ ኮሚሽኑ የላከው ደብዳቤ አምባሳደር ሽፈራው (ዶ/ር) ከሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ኮሚሽነር ሆነው እንደተሾሙ አስታውቋል፡፡ አምባሳደር ሽፈራው (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትርና ትምህርት ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደርና እንዲሁም የሌሴቶና ናሚቢያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ምንጭ Reporter @EliasMeseret

Sunday, August 7, 2022

ኢትዮጵያ የደመቀችበት

በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው የአለም ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና በውድድሩ የመጨረሻ ቀን ኢትዮጵያ የደመቀችበት፣ የማይረሳ ታሪካዊ ምሽት! 3ኛው🥇ወርቅ በ1500 ሜትር ሴቶች ብርቄ ሀየሎም 4ኛው🥇ወርቅ በ800 ሜትር ወንዶች ኤርሚያስ ግርማ 5ኛው🥇ወርቅ በ5000 ሜትር ሴቶች መዲና ኢሳ 6ኛው🥇ወርቅ በ3000 ሜትር ወንዶች መሰናክል ሳሙኤል ዱጉና 4ኛው🥈ብር በ5000 ሜትር ሴቶች መልክናት ውዱ 5ኛው🥈ብር በ3000 ሜትር ወንዶች መሰናክል ሳሙኤል ፍሬው ድንቅ ምሽት፣ ኢትዮጵያ ከፍ ያለችበት፣ በደቂቃዎች ውስጥ በተለያዩ ውድድሮች ወርቅ የጠራረገችበት ድንቅ ምሽት፣ 4 ወርቅ 2 የብር ሜዳሊያዎችን በሰዓታት ውስጥ! (via Temesgen Yifru) በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውድድሩን ከአሜሪካ እና ጃማይካ በመቀጠል በሶስተኛነት አጠናቃለች። እንኳን ደስ አላችሁ፣ አለን! ምንጭ @EliasMeseret

About Me