Facebook o girmay reda

Powered By Blogger

Followers

Tuesday, August 9, 2022

የሹመት ዜና

አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከሥልጣን በተነሱት የቀድሞ የአደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ምትክ ለአምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) የኮሚሽነርነት ሥልጣን ሰጡ፡፡ የኮሚሽኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ ኮሚሽኑ የላከው ደብዳቤ አምባሳደር ሽፈራው (ዶ/ር) ከሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ኮሚሽነር ሆነው እንደተሾሙ አስታውቋል፡፡ አምባሳደር ሽፈራው (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትርና ትምህርት ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደርና እንዲሁም የሌሴቶና ናሚቢያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ምንጭ Reporter @EliasMeseret

No comments:

Post a Comment

About Me